Welcome to
College ባለፉት 90 ቀናት 148 ሺ ለመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ከእቅድ አንፃር ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።

ባለፉት 90 ቀናት 148 ሺ ለመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ከእቅድ አንፃር ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።

01st March, 2025

ባለፉት 90 ቀናት 148 ሺ ለመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ከእቅድ አንፃር ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።
የካቲት 20/2017 ዓ ም
ከተማ አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የከተማ ግብርና የ90 ቀናት አፈፃፀምና የቀጣይ ሦስት ወራት የንቅናቄ ዕቅድ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።
ባለፉት 90 የንቅናቄ ቀናት ለ148 ሺ የከተማችን ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ለ94 935 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገልጿል።
ከሌማት ቱሩፋት አንፃር ባለፉት 90 ቀናት 151ሺ 223 አዲስ ተጠቃሚ ዜጎችን ወደ ከተማ ግብርና ማስገባት የተቻለ ሲሆን በቀጣዮቹ ሦስት ወራት 50ሺ የሚሆኑ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ወደ ከተማ ግብርና ለማስገባት በዕቅድ መያዙ ተገልጿል።
በውይይቱ በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በተሳታፊዎች ተነስተው ለቀጣይ አፈፃፀም ልምድ ሊሆን በሚችል መልኩ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የብልጽግና ፓርቲ ዋና እሳቤ ሰው ተኮርነት መሆኑን ገልፀው ለዜጎች የሥራ ዕድል ስንፈጥር እሳቤውን ተግባራዊ እያደረግን መሆኑን በማሰብ ስራውን ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥቶ መምራት ይገባል ብለዋል።
አቶ ሞገስ አያይዘውም የተመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ሦስት የንቅናቄ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አመራሩ መፍጠር እና መፍጠንን መርህ በማድረግ ጥራት ያለው ሥራ ለመስራት 24/7 መልፋት እንደሚገባው አሳስበዋል።

በመድረኩ ተገኝተው ሀሳባቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ክቡር አቶ አለማየሁ እጅጉ ሥራ ዕድል ፈጠራ በክህሎት እንዲመራ በዘርፉ ያስቀመጥነውን እሳቤ መሠረት በማድረግ ዜጎች የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን አቅም አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.