Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በብርሀን ምዘና 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ጎልማሶችና ወጣቶች ዘላቂ የሙያ ክህሎት ስልጠና ለመውሰድ ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንደሚገቡ ተገለጸ።
በብርሀን ምዘና 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ጎልማሶችና ወጣቶች ዘላቂ የሙያ ክህሎት ስልጠና ለመውሰድ ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንደሚገቡ ተገለጸ።
08th March, 2025
በብርሀን ምዘና 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ጎልማሶችና ወጣቶች ዘላቂ የሙያ ክህሎት ስልጠና ለመውሰድ ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንደሚገቡ ተገለጸ።
የካትት 27/2017 ዓ.ም
በዛሬው እለት በአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች ወደ ሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የሚገቡ ጎልማሶችና ወጣቶች የተገኙበት ፕሮግራም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና የስራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣የዘርፉ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም አመቻቾች በተገኙበት የስልጠናው ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሂዷል።
የአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛውን ትምህርት የመማር እድል ያላገኙ ጎልማሶችና ወጣቶች የብርሀን ምዘና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡት በመደበኛ ትምህርት 3ኛ ክፍል ገብተው መማር የሚችሉበት እድል ከመመቻቸቱ ባሻገር ቀጣይ ህይወታቸውን ስኬታማ ማድረግ የሚችሉበት የሙያ ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ የሚያስችል መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ጠቁመው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በ5 የሙያ መስኮች የሚሰጠው ስልጠና ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ የተዘጋጀ መርሀግብር መሆኑን በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን በጥብቅ ዲሲፒሊን በመከታተል የሙያ ባለቤት መሆን እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ በበኩላቸው የሙያ ስልጠናውን የሚወስዱ ሰልጣኞች ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው መሆኑን በመግለጽ ከነገ ጀምሮ በሚመደቡባቸው ኮሌጆች በመገኘት ስልጠናውን መከታተል እንደሚገባቸው አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ስልጠናው ለ1,750 ጎልማሶችና ወጣቶች በ5 የሙያ መስኮች ማለትም በምግብ ዝግጅት፣በውበት አጠባበቅ፣በልብስ ስፌት እንዲሁም በእንጨት ስራ እና በብረታ ብረት የሙያ መስኮች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
.