Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

08th February, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

ጥር 27/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ  ልማት ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን  ከ11ዱም ክፍለከተሞችና ከ119 ወረዳዎች ከተውጣጡ የኢንተርፕራይዝ  ቡድን መሪዎች  እና ከ15 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አስተባባሪዎች  ጋር በጋራ ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ስድስት ወራት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተደጋጋሚ መድረኮች መዘጋጀታቸው ስራዎችን ተቀራርቦ እና በባለቤትነት ለመስራት እንደሚችል ተናግረዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ  የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ  ልማት ዘርፍ  ኃላፊ  #አቶ መሀመድ ልጋኒ  መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማላቅ በቀሪዎቹ ስድስት ወራት ቀሪ ተግባራትን በተሻለ መነሳሳት እና አቅም ለመፈጸም ያስችላል ብለዋል።

ዘመናዊ የአሰራር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ከብልሹ አሰራር የፀዳ በማድረግ ሂደት ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS እንዲመዘገቡ በማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በቀጣይ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር   ለሚከናወኑ ተግባራት የባለሙያዎችን አቅም መገንባት የሚያስል ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች እና ውይይቶች እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።

.

Copyright © All rights reserved.