Welcome to
College የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ከስራ ክህሎት ጽ/ቤት ከክ/ከተማ አስተዳደሩ በጋራ የ6 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀመረ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ከስራ ክህሎት ጽ/ቤት ከክ/ከተማ አስተዳደሩ በጋራ የ6 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀመረ።

19th July, 2025

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ከስራ ክህሎት ጽ/ቤት ከክ/ከተማ አስተዳደሩ በጋራ የ6 የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀመረ።
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም(አቃቂ ቃሊቲ)
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ከስራ ክህሎት ጽ/ቤት ከክ/ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የ6 የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት መርሃ-ግብር አስጀምረዋል።
በቤት እድሳቱ መርሃ-ግብር የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ፣ የወረዳ 3 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ተሾመን ጨምሮ የወረዳው አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና መንግስት ሰው ተኮር ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ በስፋት እየሰራ እንደሚገኝና በርካቶችን ከተጎሳቆለ ኑሮ እያላቀቀ መሆኑን ጠቁመው፣ በእድሳቱ የ6ቱም ቤቶች ፈርሰው በአዲስ መልክ የሚገነባና ለዘመን መለወጫ ተጠናቆ እንደሚያስረክቡ ገልፀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሃንስ የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ስራ የብዙ አረጋዊያንን ጥያቄ የሚመልስ በነዋሪዎች የትብብር ክንድ የሚነባ እንደሆነ ገልፀው፣ ግንባታው በአንድ ወር ከግማሽ ተጠናቆ ከሙሉ የቤት ዕቃ ጭምር የሚያስረክቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የወረዳ 3 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ተሾመ በበኩላቸው መንግስት የህዝቡንና የአቅመ ደካማ ዜጎች ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚታትር ገዢ ፓርቲ መሆኑን አመላክተው፣ ተግባሩ የህሊና እርካታ የሚሰጥና በማህበራዊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ እፎይታን የሚያስገኝ መሆኑን ተናግረዋል።
.

Copyright © All rights reserved.