Welcome to
Announcement የኢራን መንግሥት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ።

የኢራን መንግሥት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ።

19th September, 2025

የኢራን መንግሥት  የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ  ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አድርገዋል።

     ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም  

የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትግበራ የላቀ ስኬት እያስመዘገበች መሆኑና ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ደግሞ የዚህ እምርታዊ ለውጥ ማሳያ  ከሆኑ ተቋማት አንዱ በመሆኑ በቀጣይ በኢራን ከሚገኙ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ጋር በትብብር ለመስራት ታቅዶ ነው ተብሏል፡፡

 አሁን ላይ በቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ ከሚገኙ ሀገራት አንዷ ኢራን ስትሆን በዚች ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር ትብብር መፍጠሩ በተግባር ተፈትኖ ውጤት ያስገኘ የካበተ ልምድና ተሞክሮ ለመጋራት እንዲሁም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ ግብዓቶችን ለማመቻቸት  ያግዛልም ተብሏል፡፡

ልዑካኑ በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ አጠቃላይ የኮሌጁን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ መረጃ በተቋሙ አመራሮችና አሰልጣኞች ገለፃ የተሰጠ ሲሆን  የተለያዩ የማሰልጠኛ ወርክ ሾፖች ምልከታ  አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ከዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ የኢራን ኢምባሲ የስራ ኃላፊዎችም መታደማቸውን ከኮሌጁ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.