Welcome to
College የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡

01st March, 2025

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡
የካቲት19/2017ዓ ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም 2ኛ ዙር አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም 3ኛ ዙር የመክፈቻ መርሃ-ግብር ከዘርፉ ባለድርሻዎችና አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡
መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ 2ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ከልየታው ጀምሮ ስራው የተመራበት አግባብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ፕሮግራሙ ስኬታማ ሆኗል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ሰላማዊት አክለውም በ2ኛው ዙር ፕሮግራም 1384 የክፍለ ከተማችን ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ስልጠናዎችን አግኝተው ክህሎታቸውን አዳብረው ለሥራ ዝግጁ በማድረግ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ 2ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ3ኛው ዙር የስራ ላይ ልምምድ እቅድ በክፍለ ከተማው የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ በአቶ መለሰ ገ/ሚካኤል አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን 3ኛው ዙር የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በአራት ወረዳዎች ማለትም በወረዳ 6፣ 8፣ 10 እና በወረዳ 13
ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስራው ከልየታ ጀምሮ በትብብርና በቅንጅት በመሰራቱ ውጤታማ በመሆኑ ይህንኑ አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.