Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ።
01st March, 2025
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 3ኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ።
የካቲት 18/2017 ዓ ም
ብቃት የወጣቶቾ የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የ3ኛ ዙር ተጠቃሚዎች መርሃ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።
ፕሮግራሙ በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በ3ኛ ዙር መርሃ-ግብር 15ሺ የሚሆኑ የከተማችን ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚውች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 25 ዓመት የሆኑ እና በትምህርታቸው 12ኛ ክፍል የደረሱ ወይም ትምህርታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያቋረጡ መሆን እንዳለባቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በመድረኩ የሚመለከታቸው የከተማ እና የክ/ከተማ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና የምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሠ 3ኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የአለም ባንክ ባስቀመጠው መስፈረት መሠረት እንዲፈፀም አቅጣጫ ሰጥተዋል።
አቶ አስፋው አያይዘው ባስተላለፉት መልዕክት በወረዳ ደረጃ ከሚገኙ የልየታና የቅሬታ ኮሚቴዎች ጀምሮ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል ።
.