Welcome to
College በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የቀጣይ የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ ተጠናቀቀ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የቀጣይ የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ ተጠናቀቀ

14th December, 2024

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የቀጣይ የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ ተጠናቀቀ
ላፍቶ ታህሳስ 3/2017:- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር "የስራ ባህልና ምርታማነትን ማሻሻል" በሚል የቀጣይ የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል።
በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ከብሎክ ጀመሮ ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር ሲካሄድ የነበረው የስራ እድል ፈጠራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ መድረክ በክፍለ ከተማ ደረጃ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶችና ሴቶች ተገኝተዋል።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በቂ ግንዛቤና እውቀት እንዲይዙ ከማድረግ አኳያ መድረኩ የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።
አቶ መብራቱ አክለውም የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመጥቀስ ይህም ንቅናቄ የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
የተሰጠውን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየርና ስራን ሳያማርጡ በተገኘው ፀጋ ላይ በመስራት እራስን መቀየር እንደሚገባ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬ የስራ ባህልን በማሻሻልና ስራን ሳያማርጡ በተገኘው የስራ አማራጭ ላይ በመስራት ያሉብንን የኢኮኖሚ ችግሮች መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
አቶ ድላየሁ ጨምረውም ከዚህ በፊት ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ሲሰጡ የነበረ መሆኑን በመጠቆም አሁን ግን ትኩረት መደረግ ያለበት ገበያው በሚፈልገው የስራ አማራጮች ላይ ሰልጥኖ ለመሰማራት መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አለም አዝብጤ በበኩላቸው ሴቶችን አሰልጥኖና አብቅቶ አቅማቸው በሚፈቅደው የስራ መስክ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ ከማድረግ አኳያ በልዩ ትኩረት ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል
.

Copyright © All rights reserved.