Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት 271ሺ 173 ለሚሆኑ የከተማችን ስራ ፈላጊ ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት 271ሺ 173 ለሚሆኑ የከተማችን ስራ ፈላጊ ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
16th April, 2025
በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት 271ሺ 173 ለሚሆኑ የከተማችን ስራ ፈላጊ ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም
የፓርቲና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራ እና የሁለተኛው ዙር የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ተገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ አበይት ተግባራት እና የሁለተኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ስራዎችአፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ባለፉት ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀናት 271ሺ 173 ለሚሆኑ የከተማችን ስራ ፈላጊ ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዕቅዱን 102% ማከናወን መቻሉን ከመድረክ ተገልጿል።
የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች 216ሺ 659 የሚሆኑት የልል እና የቴክኒካል ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በተፈጠረው የስራ ዕድል 9ሺ 228 አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ተመስርተው ወደ ሥራ መግባታቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የውይይት መድረኩ ስራው እየተመራበት ያለበትን አግባብ በመገንዘብ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ይረዳል ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከወጣቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ጽ/ቤት ም/ኃላፊና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በስራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን በመግለፅ አሁንም የወጣቶች አመለካከት ቀረፃ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜያት ከኢንተርፕራይዝ ምስረታ፣ ብድር አቅርቦት ፣በድጋፍ የሚሰጡ ሼዶችን በፍትነት ወደ ስራ ከማስገባት እና ሶስተኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በስኬት እንዲጠናቀቅ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
.