Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የሥራና ክህሎት ቤተሰብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የሥራና ክህሎት ቤተሰብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡
12th July, 2025
የቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የሥራና ክህሎት ቤተሰብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡
በወረዳ 11 አይሲቲ ፓርክ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐግብር ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባደረጉት ንግግር ዓለም በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የአየር ንብረት ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ አውስተው፣ ይህንን ችግር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ይፋ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን አመልክተዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት 2.9 ከመቶ ብቻ የነበረው የአዲስ አበባ የደን ሽፋን ከአረንጓዴ አሻራ መጀመር በኋላ ወደ 23
ከመቶ ማደጉን ያመለከቱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ አንድ ከተማ ሊኖረው የሚገባውን 30 ከመቶ የደን ሽፋን ለማሟላት በሚደረገው ርብርብ በዘንድሮው ሰባተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በክፍለ ከተmው ለመትከል የታቀደውን ከ160,000 በላይ ችግኞች የመትከል ተግባር በነቃ ተሳትፎ ለማከናወን የሥራና ክህሎት ቤተሰቦች ላደረጉት አስተዋጽኦ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ኃይሌ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦው በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸው፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራና ክህሎት ቤተሰቦች በ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን እንዳሳረፉ ሁሉ ችግኞችን በመንከባከብ ረገድም በግንባር ቀደምነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ አመራሮች፣ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ የሥራና ክህሎት ዘርፍ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
.