Welcome to
College የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከአጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር ገመገመ

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከአጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር ገመገመ

19th July, 2025

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከአጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር ገመገመ
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት አካሂዷል። በዚሁ መድረክ ላይ ኮሌጁ በበጀት ዓመቱ የፈጸማቸውን በርካታ ተግባራት በመገምገም ለቀጣይ በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ትምህርት የወሰደበት መድረክ ፈጥሯል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ የኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ጌጤነሽ ዘርአብዛ እንደተናገሩት፣ ኮሌጁ ባለፈው በጀት ዓመት ያስቀመጣቸውን እቅዶች መሰረት በማድረግ በርካታ ስራዎችን የፈጸመ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት የመደበኛ ሰልጣኝ ቅበላ፣ የሪፎርም ስራዎች እንዲሁም በርካታ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት መፈጸም እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
በግምገማው ላይ የተሳተፉ አሰልጣኝና የአስተዳደር ሰራተኞች በበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ላይ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን አንስተው ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት መሠረት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች በማብራራት በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሀሳብና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ማህበረሰብ በቀረቡት ግብዓቶች ላይ ተመስርቶ የቀጣይ ዓመት እቅዱ አፈጻጸሙን ይበልጥ እንደሚያጠናክርና ለተፈጻሚነቱም በትጋት እንደሚሰራ አስታውቋል።
.

Copyright © All rights reserved.