Welcome to
College በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የምዘና ቡድን የ2017 በጀት ዓመት ምዘና ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ።

በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የምዘና ቡድን የ2017 በጀት ዓመት ምዘና ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ።

19th July, 2025

በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ የምዘና ቡድን የ2017 በጀት ዓመት ምዘና ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ሰጠ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ የምዘና ቡድን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ሲያካሂድ የቆየውን ምዘና ማጠናቀቁን ተከትሎ የቃል ግብረ መልስ ተሰጥቷል ።
የምዘና ቡድኑ ለሰዓታት የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሪፓርቶች ሰነድ በመፈተሽ እና ምልከታ በማድረግ ከተቀመጡ መመዘኛ መስፈርቶች አንፃር ከቢሮው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ጋር በውይይት የማዳበር ተግባር አከናውኗል።
በምዘናው ሂደት ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት ሊያከናውን ያቀዳቸው ተግባራት የታለመላቸውን ዓላማ ስለማሳካታቸው በጥልቀት በመፈተሽ በጥንካሬና በድክመት እንዲሁም ትምህርት የሚወሰድባቸው ነጥቦች ላይ የምዘና ቡድኑ የቃል ግብረ መልስ ሰጥቷል።
የምዘና ቡድኑ የቢሮውን የ2017 በጀት ዓመት ጥቅል አፈፃፀም በመመልከት የሰጠው የቃል ግብረ መልስ ለቀጣይ ስራዎች መነሳሳትን እንደሚፈጥር የገለፁት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስፋው ለገሰ የበጀት ዓመቱን አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ለቀጣዩ የ2018 በጀት ዓመት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
.

Copyright © All rights reserved.