Welcome to
College የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 ዓ ም የማዕከል፣ የክ/ከተሞች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የግማሽ ዓመት የKPI ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 ዓ ም የማዕከል፣ የክ/ከተሞች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የግማሽ ዓመት የKPI ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ይፋ አደረገ።

05th April, 2025

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 ዓ ም የማዕከል፣ የክ/ከተሞች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የግማሽ ዓመት የKPI ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ይፋ አደረገ።
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወነው KPI 9ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና መሰረት በቢሮው ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና ክፍለ ከተሞች ደረጃ ይፋ ሆኗል።
የከተማ አስተዳደሩ እያከናወነ ላለው ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ተቋማቱ በቅንጅት በመስራታቸው በዘርፉ አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን ያስታወሱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር #አቶ ጥራቱ በየነ የተቋማቱን አፈፃፀም መሰረት ያደረገ ምዝና በማድረግና በደረጃ መፈረጅ የእርስ በእርስ ፉክክርን በማዳበር ለሻለ አፈፃፀም እንዲተጉ ያስችላል ብለዋል።
በዚህም መሰረት በKPI በተቀመጠው መመዘኛ መስፈርት ከክፍለ ከተሞች ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች እንደ ቅደም ተከተላቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።
በፖሊ ቴክኒክ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በተካሄደው ምዘና መሰረት አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።
በሌላ በኩል በኮሌጆች መካከል በተካሄደው ምዘና ኮልፌ እና የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጆችን በማስከተል ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ አንደኛ ደረጃን ይዟል።
በዛሬው ዕለት ይፋ ከተደረገው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እና ክፍለ ከተሞች ደረጃ በተጨማሪ በሥራና ክህሎት ቢሮ የሚገኙ የአላማ ፈፃሚ ዳይሬክቶሬቶችና የአስተዳደር ክፍሎች ደረጃ ይፋ ተደርጓል።
.

Copyright © All rights reserved.