Welcome to
College በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸውን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በማስመረቅ ለአገልግልሎት ክፍት ተገርጓል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸውን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በማስመረቅ ለአገልግልሎት ክፍት ተገርጓል

19th July, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸውን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በማስመረቅ ለአገልግልሎት ክፍት ተገርጓል
በከተማው ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት ትውልድን ለማነፅ ለሚደረገው ጥረት ይህ ተግባር ትልቅ አቅም እንደሆነ ተገለፀ።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ትውልድን ለማነፅና በየጊዜው እያደገ የመጣውን የህዝቡን አዳጊ የመልማትና የልማት ፍላጎት ለማሟላት ለነገ አገር ተረካቢ የተማረ ዜጋ ለማፍራት ወሳኝ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
ተተኪ ትውልድ ላይ መስራት ሀገር ላይ መሰራት እንደሆነ የገለፁት አቶ አብርሃም ትምህርት ተቋማትን መገንባትና መሰራት ትውልድ ላይ መስራት ነው ብለዋል።
ዛሬ ያስመረቅነው ፕሮጀክት ትውልድን ለመቅረጽ የማይተከ ሚና አለው በማለት ትውልድን መቅረጽና አብሮ መሰራት ለብልፅግናችን እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አብርሃም ታደሰ አያይዘው ብልፅግና ፓርቲ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ ማሳያ ነው ብለዋል።
ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገትና ልማት ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው የትምህርት ተቋማት ላይ ከማህበረሰብ ጋር በጋራ በመስራት የላቀ ውጤት ለማምጣት የመንግስት እያደረገ ያለው ሚና የላቀ መሆኑ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ የሚጠብቅባቸውን የየራሳቸውን ድርሻ ማበርከት ከቻሉን እና መንግስት መደገፍ የሚገባውን ካደረግ በሁሉም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አቶ አብርሃም አንስተዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት ዛሬ ከተማ አስተዳደሩ እያስመረቀ ያለው ፕሮጀክቶች ለትውልድ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተው ድህንነት ማሸነፍ የሚቻለው ትውልድን በትምህርት በማነፅና ተግቶ በመስራት ነው ብለዋል።
ትምህርት ላይ ኢንቨስትመንት ማድረግ ከምንም በላይ የነገ አገር ተረካቢን መገንባት እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ አበባ አያይዘው ትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ በመገለጽ ዛሬ ላይ የተመረቀው ትምህርት ቤት የትምህርት ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ ያለው ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.