Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ የ2017 ዕቅድ አፈፃፀሙን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያየ።
የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ የ2017 ዕቅድ አፈፃፀሙን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያየ።
26th July, 2025
የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ የ2017 ዕቅድ አፈፃፀሙን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያየ።
ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስና ዘርፍ የ2017 ዕቅድ አፈፃፀሙን በመገምገም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱ ላይ ከዘርፉ የክፍለ ከተማ አመራርና ዳይሬክተሮች ጋር ተወያይቷል።
በውይይት መድረኩ በዘርፉ የሚገኙ የስራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፤የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የአንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት የስራ ዕድል ፈላጊ ዜጎችን በኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት በመመዝገብ በስልጠና ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ በከተማዋ በሚገኙ የስራ ዕድል ፀጋዎች ለ366ሺ44 ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።
በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን በከተማ የልማታዊ ሴፍትኔት እንዲታቀፉ በማድረግ እና በተለያዩ የአካባበቢ ልማት ስራዎች ላይ በማሳተፍ 31ሺ2 ዜጎች ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ መሸጋገራቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች እና በከተማዋ የሚገኙ ስደተኞችን ከሚደርስባቸው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመታደግ በተሰራው ስራ አበረታች ለውጥ ማምጣት መቻሉ ተመላክቷል።
በበጀት ዓመቱ አንድ ማዕከላትን ሞዴል ፍረጃ በማጠናከር ሂደት አበረታች ውጤት ማምጣት መቻሉ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታንዳርዱን የተመለከተ ጥናት ከማሰራት ባሻገር የኢትዮጵያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት ከአንድ ዳሽ ቦርድ ጋር ማስተሳሰር መቻሉ ተነስቷል።
በሌላ በኩል በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ለ350ሺ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር 15ሺ ኢንተርፕራይዞችን በ105ሺ አንቀሳቃሾች ለማደራጀት ታቅዷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ በተጠናቀቀ የ2017 በጀት ዓመት የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን በመግለፅ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ከተለመደው የአሰራር ዕይታ በተለየ መልኩ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ መትጋት ይገባል ብለዋል።
መረጃ የማጥራት ተግባሩን በማጠናከር በበጀት ዓመቱ ዜጎች በሚገባ ተጠቃሚ ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ተግባር መከናወን እንደሚገባውም አቶ አስፋው አሳስበዋል።
.