Welcome to
College የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2017 አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የተላለፈ መልዕክት፦

የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2017 አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የተላለፈ መልዕክት፦

26th October, 2024

“የቴክኒክ እና ሙያ ውጤት ተኮር ሰልጠና በመስጠት በዝቅተኛ፣መካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለኢንዱስትሪ ማቅረብ ነው። በዚሁ መሰረት ጥራት ያለው ስልጠና ለመሰጠት ኮሌጆች የISO ሰርቲፋይድ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ተጀምሯል። በዚህም አለም አቀፍ ተወዳዳሪና የሆነ የሰው ሀይል ለኢንዱስትሪ የማቅረብ ተልዕኮ በመፈፀም ላይ እንገኛለን። መሆኑም የቴክኒክ  እና ሙያ በመደበኛ መርሀግብር ለመሰልጠን ፈቅዳችሁ የመጣችሁ ወጣቶች የማሰልጠኛ ኮሌጆች ከፍተኛ ዝግጀት አድረገው እናንተን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 ድረስ በሀገር አቀፍ የመቁረጫ ነጥብ መሰረት በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና በ14 የመንግስት ኮሌጆች ይሰጣል። 2017 አዲስ ሰልጠኝ ምዝገባ ለየት የሚያደርገው “Online” በመሆኑ ነው። ምዝገባ ከማከናወናችሁ በፊት በአቅራቢያችሁ ባሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚሰጡ የሙያ አይነት፣ ደረጃና ፍላጎት በመምረጥ ይመዝገቡ። ምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 15-24/2017 ድረስ ሲሆን ቀድሞ መመዝገብ ይመከራል።”

ዶክተር አበራ ብሩ

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ

.

Copyright © All rights reserved.