ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ20ኛው ግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሻለሚ ሆነ።
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ20ኛው ግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሻለሚ ሆኗል።
ኮሌጁ በአመራር ጥበብ፣በማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች፣በዲጂታላይዜሽን እንዲሁም በሌሎች በርካታ ነጥቦች የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቡ ነው የፕላቲኒየም ደረጃ ተሻለሚ የሆነው።
በሽልማት መርሐ- ግብሩ ከ1 ሺህ 250 በላይ ተቋማት የተመዘኑ ሲሆን፣ በሦስት ደረጃዎች የፕላትኒዬም፣የዳይመንድ እና የወርቅ ደረጃ ሜዳሊያ ተሸላሚ ናቸው።
በመረሐ- ግብሩ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት እና የግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌደራል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በገኙበት የንፋስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕላቲኒየም ደረጀ ተሻለሚ በመሆን ከቀድሞ ኘሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እጅ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ሸለማ ንጉሱ ተቀብለዋል።
ትጉኃንን እንሸልማለን" በሚል መሪ ሀሳብ በሚከናወነው የሽልማት መርሐ-ግብር አገልግሎት ሰጪ እና አምራች የሆኑ የግል፣ የመንግስት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ዕውቅና ያገኛሉ።


.