Welcome to
College ባለፉት ወራት ከ19 ሺህ በላይ ስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገለፀ።

ባለፉት ወራት ከ19 ሺህ በላይ ስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገለፀ።

22nd February, 2025

ባለፉት ወራት ከ19 ሺህ በላይ ስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገለፀ።
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው አስተዳደር ስራና ክህሎት ፅ/ቤት የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም በመገምገም የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አካሄደዋል።
በመርሀ ግብሩ ፅህፈት ቤቱ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸውን የሪፎርም ስራዎች፣ የኢኒሸቲቭ ስራዎች፣ ቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ የተሰሩ የገበያ ትስስር፣ የብድር አሰጣጥና ማስመለስ፣ የኤግዚብሽንና ባዛሮች አፈፃፀም፣ በስራ ስምሪት ዘርፍ የተከናወኑ ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት፣ የስራ ፈላጊዎች ምዝገባ፣ ስልጠና፣ ግንዛቤ ፈጠራና የፀጋ ልየታ እስከ ስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ፣ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም፣በኢንዱስትሪዎች የአሰሪና ሰራተኛ የነበሩ አፈፃፀሞች በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሒዶበታል።
አቶ ኢብራሒም መሀመድ የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ እንደገለፁት ፅ/ቤቱ የተሳካ የሪፎርም ስራዎች በማከናወን ክህሎት መር የስራ አድል በመፍጠር ለ19ሺህ 6መቶ 80 ወጣቶችና ሴቶች ስራ እድል መፈጠሩን ገልፀው በቀጣይም የስልጠና የስራ እድል ፈጠራና አንቀሳቃሾችን ቁጥር የማስፋትና የስራ እድል ፈጠራውን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ልሳነወርቅ ጣሰው በበኩላቸው የመድረኩ ዋና ዓላማ ክፍተቶቻችንን በማረም የተሻሉ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑን ገልፀው በቀሪ ወራት የተቀሩ ስራዎች ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
በመርሀ ግብሩ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ቡድኖች ባለድርሻ አካላትና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በተደረገው የወረዳዎች አጠቃላይ ምዘና ወረዳ 09፣ 01 እንዲሁም ወረዳ 08 እና 11 በተመሳሳይ ውጤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆናል።
.

Copyright © All rights reserved.