Welcome to AATVETB College
Announcement የ16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደ-ርዕይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

የ16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደ-ርዕይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

08th May, 2026

የ16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደ-ርዕይ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

🇪🇹አዲስ አበባ | ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም🇪🇹

ላለፉት ቀናት በአራዳ ፓርክ "የቴክኖሎጂ ልህቀት ለአገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደ-ርዕይና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ዛሬ በደመቀ ስነ-ስርዓት ተጠናቋል።

በማጠቃለያው ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ፤ የቴክኖሎጂ ታሪክ የኢኮኖሚ ልማት ታሪክ መሆኑን በጥልቀት በመተንተን፣ ባለፉት ቀናት የቀረቡት የፈጠራ ስራዎች የሀገሪቱን የልማት ተስፋና ተጨባጭ እንቅስቃሴ የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል። መንግስት የክህሎት መር የሥራ ስምሪትን እንደ ዋነኛ ፖሊሲ በመከተሉ፣ ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም በተግባር እንዲያሳዩና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ራሳቸውን በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ-ምግባር በማነጽ ለሀገራቸው ብልጽግና እንዲተጉ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አብራርተዋል። አክለውም፣ ወጣቶች የሥራን ክብር በመረዳትና ዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ የሀገር ግንባታ አካል እንዲሆኑና የጀመሩትን የፈጠራ ስራ ወደ ቢዝነስ በመቀየር ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አደራ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በበኩላቸው፣ የዘንድሮው አውደ-ርዕይ ቴክኖሎጂዎችን ለዕይታ ብቻ ከማቅረብ ባለፈ በቀጥታ ወደ ፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግ በማሸጋገር ለተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያስችል አዲስ ስትራቴጂ የተተገበረበት መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የውጭ ምንዛሬን የሚያድኑ ተኪ ምርቶችን ማምረት እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጡበት መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዕለቱ በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በዲጂታል  አይሲቲ ቴክኖሎጂዎች ፈጠራ፣ በፋሽን ዲዛይን ፤ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ከፍተኛ ውጤት እንዲሁም በ ስፖርት ዉድድር አሸናፊ በመሆን በደረጃ ለወጡት  የእውቅና እና የሽልማት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። የተጀመረው የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምርት መተካት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል። 

.

Copyright © All rights reserved.