Welcome to
+
|
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
College
News
Office Head Message
More
Registration Guideline
User Manual
CoC Result
Login
College
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 15ኛውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 15ኛውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።
14th June, 2025
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 15ኛውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው 15ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት ቢሮው አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን ገልጿል።
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንና ገበያ ልማት ማዕከል በሚካሄደው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በኮሌጅና በክላስተር ደረጃ በተካሄደ ውድድር የቀረቡ ከ187 በላይ በአሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች የተቀዱ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ጨምሮ 77 የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሁም ከ500 በላይ ሰልጣኞች በ19 የሙያ አይነቶች ውድድር እንደሚያደርጉ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ
#አቶ
መሀመድ ልጋኒ ተናግረዋል።
የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ምርት በማስገባት የፈጠራ ባለሙያዎችን እንደሚያበረታታ የተገለፀ ሲሆን በሌላ በኩል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች በክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ የበቁ ዜጎችን ለገበያው በማቅረብ ሂደት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማስገንዘብ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ ዘርፉን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ የገለፁት አቶ መሀመድ በቴክኒክና ሙያ ማህበረሰቡ መካከል ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችሉ ስፓርታዊ ውድድርና የፋሽን ሾው ትርኢት ይካሄዳል ብለዋል።
ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 12 2017 ዓ.ም የሚካሄደውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክ ሙያ ሳምንት የከተማዋ ነዋሪ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንና ገበያ ልማት ማዕከል በመገኘት በነፃ መጎብኘት እንደሚችል በመግለጫው ተመላክቷል።
.