Welcome to
College የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበት ደረጃ የግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡

የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበት ደረጃ የግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡

14th June, 2025

የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበት ደረጃ የግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደርዕይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች ጋር በጋራ ገምግሟል፡፡
በግምገማ መድረኩ በቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ የሚካሄዱ ሁነቶች የደረሱበት ደረጃ እና የሚካሄዱበት አግባብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በዚህም የኮሌጆችን የመልማት ጸጋ መሰረት በማድረግ በተካሄደው የዞኒንግና ዲፈረንሼን መሰረት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሰልጣኞችና ሰልጣኞች የተቀዱ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊነት ፍተሻና ልየታ መካሄዱ ተነስቷል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለውን አመለካከት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ መርሃ ግብሩ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ የዘርፉን እሳቤ በማስረጽ የ2018 ዓ.ም ሰልጣኞች ቅበላ በማሳደግ ሂደት ሚናው የጎላ መሆኑንም አቶ ጥራቱ ተናግረዋል፡፡
ከቴክኖሎጂ ውድድሩ ጎን ለጎን ዘርፉን በሚያልቁ የተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የፋሽን ሾው እና ስፖርታዊ ውድድሮች በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል፡፡
15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንና ገበያ ልማት ማዕከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
.

Copyright © All rights reserved.