Welcome to
Announcement የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ከ1.4 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ።

የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ከ1.4 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ።

05th September, 2025

በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  በኮሌጁ አሰልጣኞች  የተቀዱ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ከ1.4 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ኮሌጁ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር እና የቴክኒክና ሙያ ሳምንት 8 ችግር ፈቺ የምርት፣የማምረቻ እንዲሁም ሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት እያሸጋገረ እንደሚገኝ የኮሌጁ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን አቶ ባህሩ ሻፊ ተናግረዋል።

የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የሚያቀሉና ስራን በማሳለጥ ረገድ አውንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችሉ የማምረቻ ቴክኖሎጂዎች ለኮሌጁ ኢንተርፕራይዝ  በብድር ውል  በማሸጋገር  ወደ ብዝሀ ምርት ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ኮሌጁ የማክሮ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ተኪ ምርቶችን በማቅረብ እና የኮሌጁን ማህበረሰብ ከኢኮኖሚያዊ ጫና በመታደግ ሂደት ሰባት የምርት ቴክኖሎጂዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለኮሌጆ ማህበረሰብ  በብድር ማቅረብ   መቻሉንም አቶ ባህሩ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በሀገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ በተካሄዱ ውድድሮች ኮሌጁን ብሎም የከተማ አስተዳደሩን ግንባር ቀደም እንዲሆን ካስቻሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንድ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ  ወደ ስራ ለማስገባት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ዲዛይንና አዋጭነት አስተባባሪ አቶ ደረጄ መንግስቴ በበኩላቸው  የኢንተርፕራይዞችን ፍላጎት መነሻ አድርጎ በተሰራው የቴክኖሎጂ ስራ  ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረዋል።

በቅርቡ በዘርፉ የተካሄደውን ሪፎርም ተከትሎ በኮሌጁ የተቋቋመው ኢንተርፕራይዝ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት በኮሌጁ የሚቀዱ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደ ብዝሀ ምርት በማስገባት ሀብት ማፍራት እንዲችል  የፋብሪኬሽን ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ዲኑ ጨምረውም ገልጸዋል።

ከቴክኖሎጂ ስራው ጎን ለጎን የክህሎት ባንክ በመገንባት ይህም ቴክኖሎጂ የሚታይበትና ልምድ የሚቀሰምበት ማዕከል በመሆን ያገለግላል ተብሏል።

                                                      ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

<<ከፍታን ማፅናት፤ ነገን ማላቅ>>


.

Copyright © All rights reserved.